በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

5
ባሕር ዳር: መጋቢት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መጋቢት 24/ 2010 ዓ.ም የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ባለፉት ስምንት ዓመታት በለውጡ መንግሥት የተመዘገቡ ስኬቶችን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል ተብሏል።
የለውጡ መንግሥት በተለይ በፖለቲካ ዘርፍ አካታች የፓለቲካ ምዳር መፍጠሩም ተገልጿል። ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ አሳሪ የሚኾኑ ሕጎችን በማሻሻል ገዥ ትርክት የመገንባት ሥራ በትኩረት ተሠርቷል።
ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት ምሰሶ የኾኑ ዘርፎችን በመለየት በተከናወነ መጠነ ሰፊ ሥራ አበረታች ውጤት መመዝገቡም ተገልጿል።
ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው አንድነትን በማጠናከር የተመዘገቡ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባ ተመላክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የትግራይ ክልልን ዓመታዊ አፈጻጸም ገመገሙ።
Next articleአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።