የነዳጅ ማደያዎችን አገልግሎት በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚዘዋወረው መረጃ ልክ ነውን?

3
ባሕር ዳር:መጋቢት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክኒያቱን የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ያደረገው የነዳጅ እጥረት ወዲህም ፈተና አብዝቷል። ነገር ግን የተፈጠረው ችግር እንዳይባባስም የተለያዩ መፍትሄዎች እየተወሰዱ ነው።
እንደመፍትሄ አካል ኾኖ በባሕር ዳር የሚገኙ ማደያዎች የተመደበላቸውን ተሸርካሪ ብቻ እንዲያስተናግዱ የሚያስገድድ አዲስ አሠራር መውጣቱን የተመለከተ መረጃ እየተሠራጨ ይገኛል።
#መረጃው ልክ ነውን?
የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፈንታው ፈጠነ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት የሚሰጡት በአዲስ አሠራር ነው ብለዋል። አሠራሩ በዋነኝነት ትኩረቱን ያደረገው በከተማዋ የሚታየውን የነዳጅ ሥርጭት ሥርዓት ለማስያዝ እና አገልግሎቱን ቀልጣፋ ለማድረግ መኾኑንም አንስተዋል።
ምክትል ኀላፊው እንዳሉት የአሠራሩ ዋና አላማ “ቅድሚያ ማግኘት ያለባቸው” ተሽከርካሪዎች በቅደም ተከተል አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ይህም የፌዴራል መንግሥት ያስቀመጣቸውን መመሪያዎች እና ነጥቦች መሠረት በማድረግ የሚከናወን መኾኑን ጠቁመዋል።
የነዳጅ አገልግሎት አሠጣጥ ሂደቱ በባሕር ዳር ከተማ በሚገኙ ማደያዎች ላይ በየቀኑ የሚወጡ መመሪያዎችን መሠረት ያደረገ እና እንደ ኹኔታው በየቀኑ ሊለወጥ እንደሚችልም ጠቁመዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የተጠናከር የሕግ የማስከበር ሥራ እየተሠራ ነው” ኮሚሽነር ጄኔራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ.ር)
Next articleየልብ ሕመም ይድናል ?