ለውጡ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ ነው።

3
ባሕር ዳር: መጋቢት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ)በሐረር ከተማ በሀገራዊ ለውጡ የተገኙ ድሎች እና ስኬቶችን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ በክልሉ ከገጠር እና ከከተማ የተውጣጡ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል። በሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ መልዕክት ያስተላለፉት
የሐረሪ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት ታላላቅ ሀገራዊ እና ክልላዊ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
ለውጡ በተለያዩ የልማት መስኮች ድል ለማስመዝገብ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈተ መኾኑን ገልጸዋል። ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እና ብሔራዊ መግባባት የተፈጠረበት ሀገረ መንግሥት በመገንባት ላይ መኾኑን ተናግረዋል።
የለውጡ ዓመታት ጠንካራ የአመራር ውህደት የተፈጠረበት እና ከፍተኛ የልማት መነሳሳት የታየበት መኾኑን ገልጸው። የሕዝብ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት የተረጋገጠበት ነው ብለዋል።
በዚህም የለውጡ መንግሥት ሀገር መምራት ከጀመረበት ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች እመርታዎች መመዝገባቸውን አመልክተዋል።
ሕዝቡ ሀገሪቷ የጀመረችውን ሁሉ አቀፍ የልማት ሥራዎችን እንዲደግፍም አስገንዝበዋል።
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ ለመራጭነት የሚያበቃውን የምርጫ ካርድ በመውሰድ በንቃት መሳተፍ እንደሚገባም ተናግረዋል።
የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ጌቱ ወዬሳ መጋቢት 24 በታሪክ አጋጣሚ የተከሰተ ሳይኾን በሕዝብ ትግል እና መስዋዕትነት የመጣ የድል ፍሬ ነው ብለዋል።
መጋቢት 24 በኢትዮጵያ ኢ ፍትሐዊ ሥርዓት ከሕዝብ ጫንቃ ላይ የተነሳበት፤ በአዲስ አስተሳሰብ፣ በአዲስ እይታ አካታች፣ ኅብረ ብሄራዊ፣ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት የተጠናከረበት መኾኑን ገልጸዋል።
ከሐረሪ ክልል ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማዕከል ያደረገ የመደመር መንግሥት የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት ታሪካዊ ቀን ነው ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሰሙነ ሕማማት እና ምስጢሮቹ
Next articleለአፍሪካውያን በራሳቸው አቅም የአደጋ ስጋት ሥራዎችን መደገፍ የሕልውና ጉዳይ ነው።