
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 26/2018 ዓ.ም(አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ በአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ከፓፒረስ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ እስከ ዲያስፖራ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚዘልቅ የ3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ እና የኮሪደር ልማት ሥራ ተጀምሯል።
በማስጀመሪያው ላይ የተገኙት የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የኮሪደር ልማት “ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ ለመገንባት” የሚያስችል መኾኑን ተናግረዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ ሥራው ዜጎች በንጹህ አካባቢ የመኖር መብታቸውን የሚያረጋግጥ መኾኑንም ገልጸዋል።
የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ልማቱ የከተማዋን ኢኮኖሚ እንደሚያነቃቃ እና የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ ተናግረዋል።
ልማቱ ዘመናዊ የከተማ ገጽታ ከመፍጠር ባለፈ ለእግረኞች ደኅንነት እና ለነዋሪዎች ምቹ አየር እንዲኖር ያስችላል ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
