አሚኮ ባለሙያዎቹ በምቾት እንዲሠሩ የሚተጋ ተቋም ነው።

7

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለሦሥት የአካል ጉዳተኛ ሠራተኞች የሦሥት እግር ተሽከርካሪ ድጋፍ አድርጓል።

የድጋፉ ተጠቃሚ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሞላ እንደተናገረው ወደ ሥራ ለመምጣት ከአካል ጉዳተኝነቱ አንጻር ብዙ ይቸገር እንደነበር ተናግሯል። አሁን ግን ይገጥመው የነበረው ችግር በመቀረፉ አሚኮን አመሠግናለሁ ብሏል።

የአሚኮ ሌላው የአካል ጉዳተኛ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ዋሴ ሞተሩን ከማግኘቱ በፊት የአሚኮ የሠራተኞች ሰርቪስ ይጠቀም የነበረ ቢኾንም ከአካል ጉዳተኝነቱ አንጻር ሰርቪሱ ላይ እስኪደርስ ብዙ ይቸገር እንደነበር ጠቁሟል።

አሁን ላይ አሚኮ የሠራተኞቹን ምቾት ሲጠብቅ እሱም ተጠቃሚ መኾኑ እንዳስደሰተው አብራርቷል። ሌሎችም ተቋማት የአሚኮን ልምድ ወስደው ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኞቻቸው አስፈላጊውን እገዛ ቢያደርጉ ብሏል። አሚኮ ስላደረገለት እገዛም አመሥግኗል።

ጋዜጠኛ ዋለልኝ ክንዴም የአካል ጉዳቱ በሥራው ላይ እና በእሱም ላይ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ አሚኮ ተረድቶ ላደረገለት እገዛ ምሥጋና አቅርቧል።

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ጋዜጠኛ መሰረት አስማረ አሚኮ ለኅብረተሰብ ለውጥ የሚተጋ ተቋም ነው፤ ይህንንም በተለያዩ የዘገባ ሥራዎቹ እያሳየ ነው ብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እና ምቾት መትጋት ከራስ ይጀምራል፤ የራሳችንን ቤተሰቦች ማገዝ ማኅበረሰቡን ማገዝ ነው ብለን እናምናለን ነው ያለው።

ሁሉም የቅርቡን ማገዝ ቢችል ችግሮችን በቀላሉ መቅረፍ እንችላለን፤ አሚኮ ለሠራተኞቹ ሞተሮችን የገዛውም በረጅም ጊዜ ብድር ስለመኾኑ ገልጿል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል መንግሥት ለ1ሺህ 224 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።