ዋና ዋናዎቹ የዲጂታል ፋይናንስ ማጭበርበሮች፦

5

 

ባሕር ዳር: መጋቢት25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዲጂታል ፋይናንስ ማጭበርበር ማለት የዲጂታል መሳሪያዎችን በመጠቀም ሰዎችን በማታለል፣ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት፣ የክፍያ ሥርዓቶችን በመጣስ እና መረጃ በመስረቅ ያልተገባ የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት የሚፈጸም ወንጀል ነው።

ዋና ዋና የማጭበርበር የትኞቹ ናቸው?

✍️ማኅበራዊ ማጭበርበር (Social Engineering/Phishing)፦

ወንጀለኞች የሠዎችን ሥነ ልቦናዊ ክፍተት (እንደ ፍርሃት፣ ጉጉት ወይም ሥግብግብነት) በመጠቀም ሚስጥራዊ የባንክ መረጃዎችን (የይለፍ ቃል፣ የሂሳብ ቁጥር) እንዲሰጧቸው የሚያደርጉበት መንገድ ነው።

✍️በውስጥ ሠራተኞች የሚፈጸም ማጭበርበር፦

ይህ ደግሞ በባንክ ወይም ቴሌኮም ተቋማት ውስጥ ባሉ ግለሰቦች የሚፈጸም ነው። የተዘጉ ሂሳቦችን በማንቀሳቀስ፣ ሲስተሞችን አላግባብ በመጠቀም፣ የደንበኞችን ፒን ኮድ (Pin code) ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ በመስጠት እና መረጃ በማውጣት የሚፈጸም ወንጀል ነው።

✍️የሲም ካርድ ማጭበርበር (SIM Swap)፦

አጭበርባሪዎች የግለሰቦችን የባንክ ስልክ ቁጥር ከእውቅና ውጪ በማዘጋት እና ምትክ ሲም ካርድ ያወጣሉ። በመቀጠልም የሞባይል ባንኪንግ የይለፍ ቃልን በመቀየር የደንበኞችን ገንዘብ ይሠርቃሉ።

✍️የሞባይል ባንኪንግ ማጭበርበር፦

የግለሰቦችን ሞባይል ስልክ በመሥረቅ፣ ሐሰተኛ ማንነትን በመጠቀም እና መተግበሪያዎችን አላግባብ በመጠቀም የሚፈጸም የገንዘብ ሥርቆት ነው።

✍️የሞባይል ዋሌት ማጭበርበር፦

ይህ ወንጀል በብዛት ሊፈጸም የሚችለው ደንበኞች ደካማ የይለፍ ቃላትን ሲጠቀሙ፣ ያልተረጋገጡ አፕሊኬሽኖችን ሲጭኑ፣ እንዲኹም ፒን (PIN) እና ኦቲፒ (OTP) መረጃዎችን ለሌላ ሰው ሲያጋሩ እንደኾነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር መረጃ ያሳያል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበግብርናው ዘርፍ ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል።
Next articleየአማራ ክልል መንግሥት ለ1ሺህ 224 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።