የሀረሪ ክልል አሥተዳደር ምክር ቤት አዲስ የበጀት ክለሳን አጸደቀ።

4

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሀረሪ ክልል አሥተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የ2018 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የቀረበለትን የበጀት ክለሳ አጽድቋል።

ሥራ አሥፈጻሚው በክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አማካኝነት የቀረበለትን 523 ሚሊዮን 603 ሺህ 565 ብር የበጀት ክለሳ ነው ተወያይቶ ያጸደቀው።

የበጀት ክለሳው ያስፈለገው በተለይም የፊዚካል እና ፋይናንሻል አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ የኾኑ ፕሮጀክቶችን በመለየት የላቀ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ፋይዳ ላላቸው እና የበጀት እጥረት ላጋጠማቸው ጉዳዮች ለማዋል ነው ተብሏል።

የበጀት ክለሳው ለገጠር ሞዴል የአርሶ አደሮች ቤት ግንባታ ፕሮጀክት፣ ለገጠር ትስስር ተደራሽነት፣ ለምግብ ዋስትና እና ለመደበኛ ሥራዎች ማሥፈጸሚያዎችን በመለየት የበጀት እጥረት ላጋጠማቸው ጉዳዮች እንደሚውል ተገልጿል።

ሥራ አሥፈጻሚው የቀረበለትን የበጀት ክለሳ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።

ከሀረሪ ክልል ኮሚዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጣል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበፎቶ ወይም ሥም አማካኝነት የሚስተዋሉ ሥርቆቶችን የሚያስቀረው የባዮሜትሪክ ማንነት ማረጋገጫ።