በአዲስ የተሻሻለ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ የሕግ መድብል ጸደቀ!

3

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 25/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ኾኖ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል።

ባለፉት የሪፎርም ዓመታት ሕገ መንግሥታዊነትን ለማረጋገጥ፣ የመብቶችን ጥበቃ ለማስፋትና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የሚያስችሉ ሰፋፊ የሕግና ተቋማዊ ማሻሻያዎች የተደረጉ ሲሆን በዚህ ሒደት ከተለዩት ቁልፍ ሕጎች መካከል አንዱ የወንጀል ሥነ ሥርዓት የሕግ መድብሉ ነው።

የ1954 የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት እና ከወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት

የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። ብዙ ምክክር ተደርጎበት የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን የሚያስተዋውቅ፤ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መኾኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ጠቁሟል።

#አሚኮ #PMOEthiopia

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ተደረገ።
Next articleድጋፍ የሚሹ ወገኖች