
ባሕር ዳር: መጋቢት 24/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሀገራዊ ለውጡ እውን የኾነበት 8ኛ ዓመት የሚዘክር ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሰልፈኞቹም በመጋቢት 24 ፍሬ ወደ ተምሳሌታዊ ጉዞ፣ ጠንካራ መሠረት የተምሳሌትነት ጉዞ ስንቅ፣ መሠረት ባለው ርምጃ ወደ ተምሳሌትነት፣ መጋቢት 24 የተምሳሌታዊነታችን መሠረት እና መፍለቂያ ነው ብለዋል።
የመጋቢት 24 ፍሬዎች የተምሳሌትነት ጉዞ የትውልድ ብልጽግና ነው የሚሉ መልዕክቶችን አሰምተዋል።
በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ፣ በቀጣይም የተሻለ ሥራ እንዲሠራ ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሠሩ የሚያረጋግጡ መልዕክቶችንም አስተላልፈዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
