የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ከአካባቢው መዋቅር ጋር ተቀራርበው በመሥራታቸው ሰላማቸውን ጠብቀዋል።

7
ባሕርዳር: መጋቢት 23/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ አሥተዳደር እና ከቀወት ወረዳ ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) የሸዋሮቢት ከተማ የብዝኀነት እና የአብሮነት ከተማ መኾኗን አረጋግጠናል ብለዋል።
የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ከአካባቢው መዋቅር ጋር ተቀራርበው በመሥራታቸው ሰላማቸውን እንደጠበቁት ሁሉ በቀጣይም ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትን ወደ ሰላም እንዲመጡ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።
የሸዋሮቢት እና አካባቢው ኢኮኖሚ መነቃቃት ማሳየቱን ገልጸዋል። በቀጣይ ለኢንቨስትመንት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራ ይገባል ብለዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤሊያስ አበበ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር ተቀራርቦ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
ለልማት ሥራዎችም ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በኹሉም አካባቢ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾናቸውን አንስተዋል።
የሸዋሮቢት ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘላለም መኮንን ከተማ አሥተዳደሩ ሰላሙን በመጠበቅ በርካታ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
የሸዋሮቢት ከተማ እና የቀወት ወረዳ ነዋሪዎችም ከመንግሥት ጋር ተቀራርበው በመሥራታቸው ሰላማቸውን እያረጋገጡ መኾኑን ገልጸዋል።
ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር በጋራ የሰላም ኮሚቴዎች በኩል ተቀራርበው በመሥራታቸው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነታቸው መጠናከሩንም ጠቅሰዋል።
ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎቹ በሸዋሮቢት ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየ13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ታሪካዊ የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈርሟል።
Next articleባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወላጆቻቸውን ያጡ እና ለችግር የተጋለጡ ሕጻናትን ለማሳደግ ተረከበ።