ሚስጥራዊ መረጃን ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ከማጋራት በፊት ጥንቃቄ ማድረግ፦

7
ባሕር ዳር: መጋቢት23 /2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የዕለት ተዕለት ሥራን እያቃለለ ነው። ነገር ግን ከእድገቱ ጋር ተያይዘው የሚመጡ የሳይበር ጥቃቶች አሳሳቢ ኾነዋል።
በቅርቡ በChatGPT የሶፍትዌር ሥርዓት ላይ በተገኘ ከፍተኛ የደህንነት ክፍተት፣ ጥቃት አድራሾች በአንድ “አደገኛና አጥፊ ትእዛዝ” (Malicious Prompt) ብቻ የግልና የተቋማትን መረጃዎች መዝረፍ የሚያስችል አጋጣሚ ተፈጥሮ እንደነበር የቼክ ፖይንት (Check Point) ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል።
ይህ የደህንነት ስጋት አጥፊ የኾኑ የጽሑፍ ትእዛዞችን በመጠቀም የChatGPTን የመከላከያ አጥር በመጣስ፣ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በቀጥታ ወደ ጥቃት ፈጻሚዎች ሰርቨር (Server) ማስተላለፍ ያስችላል።
ይህም ተጠቃሚዎች ወደ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚጭኗቸውን ልዩ ልዩ ፋይሎች፣ የግል መልእክቶች እና ሚስጥራዊ የድርጅት ሰነዶች ለከፍተኛ አደጋ አጋልጦ ቆይቷል።
✍️ጥንቃቄው
👉 ትእዛዞችን (Prompts) ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ፦ በማኅበራዊ ሚዲያ ወይም በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ “ምርጥ ውጤት ያስገኛሉ” ተብለው የሚሰራጩ የትእዛዝ አይነቶችን ሳያረጋግጡ አይጠቀሙ። እነዚህ ትእዛዞች መረጃዎን በድብቅ ወደ ጥቃት ፈጻሚዎች የሚልኩ ድብቅ መመሪያዎችን ሊይዙ ይችላሉ።
👉ሚስጥራዊ ፋይሎችን ከመጫን ይቆጠቡ፦ የባንክ መረጃዎችን፣ የጤና ሰነዶችን ወይም የተቋማትን ሚስጥራዊ ፋይሎች ወደ AI ሲስተሞች ከመጫንዎ በፊት በደንብ ያስቡ።
👉ምንጊዜም ንቁ መኾን፦ ምንም እንኳን ለChatGPT የደህንነት ማስተካከያ ቢደረግለትም፣ አጥቂዎች አዳዲስ የጥቃት ዘዴዎችን መፈለጋቸውን አያቆሙም።
ስለዚህ ከማይታወቁ ምንጮች የሚመጡ “አቋራጭ መንገዶችን” ሁልጊዜም በጥርጣሬ መመልከት ይገባል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleማንነትን መሠረት ያደረገ የሳይበር ጥቃት ሥጋት፦
Next articleየገበያ ማዕከሉ የኑሮ ወድነትን የሚያቃልል እና የገበያ ትስስርን የሚፈጥር ነው።