
ባሕር ዳር: መጋቢት22/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በቅርቡ የወጡ የሳይበር ደኅንነት ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት የሳይበር ወንጀለኞች የቲክቶክ ለንግድ (TikTok for Business) አካውንቶችን ለመዝረፍ የሚያስችል አዲስ እና ውስብስብ የማጭበርበሪያ ጥቃት ሰንዝረዋል።
ፑሽ ሴኪዩሪቲ (#Push Security) የተባለው የደኅንነት ተቋም ባወጣው መረጃ መሠረት ጥቃቱ በተለይ የቲክቶክ እና የጎግል መልዕክቶች በሚመስሉ የሐሰት ገጾች አማካኝነት የሚፈጸም መኾኑን ገልጿል።
ይህ አደገኛ የሳይበር ጥቃት በሦስት ዋና ዋና ደረጃዎች የሚከናወን እንደኾነም ነው የተገለጸው።
አንደኛው ማታለያ ኢሜይል ሲኾን መጀመሪያ “የሥራ ዕድል አለ” የሚል ማራኪ መልዕክት በኢሜይል አማካኝነት ለተጠቃሚዎች ይላካል።
ሁለተኛው ጥቃት የሐሰት ድረ ገጽ ነው። በዚህ ጥቃት ተጠቃሚዎች የተላከላቸውን ሊንክ ሲጫኑ የቲክቶክ ወይም የጎግል መግቢያ ገጽ ትክክል የሚመስል ነገር ግን ሐሰት የኾነ ገጽ ይከፈትላቸዋል።
ሌላኛው ጥቃት ደረጃ የመረጃ ሥርቆት ነው። ይህ ጥቃት ደግሞ ተጠቃሚው በዚያ ገጽ ላይ የተጠቃሚ ሥም እና የይለፍ ቃሉን (Password) ሲሞላ መረጃው በቀጥታ በወንጀለኞቹ እጅ እንደሚገባ ነው ይፋ የኾነው።
ተጠቃሚዎች ከዚህ ጥቃት ራሳቸውን ለመጠበቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ ይመከራል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
