የእናቶች እምባ የሚታበሰው በፍቅርና በመቻቻል ነው!

17

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለሠላም የቆረጡ ልቦች የእውነተኛ ጀግንነት መለኪያዎች ናቸው። ጀግንነት ጠመንጃ መጨበጥ አይደለም። ትልቁ ጀግንነት ለሀገርና ለወገን ሰላም ሲባል ያንን ጠመንጃ መሬት ላይ ማስቀመጥ መቻል እና ሀገርን ማስቀደም ነው። ለመዋጋት አንድ ጣት ይበቃል፤ ሰላምን ለመገንባት ግን ሙሉ ልብና አዕምሮ ያስፈልጋል። ወደ ሰላም መንገድ የሚመጡ ደግሞ ይሄንን ያረጋገጡ ናቸው።

​👉ከጥፋት ወደ ልማት

በትናንትናው ማንነታችሁ ለጥፋት የተዘጋጀውን ጉልበት፣ ዛሬ ለሀገር ግንባታና ለትውልድ ተስፋ ለማዋል ወስናችኋል። ይህ ከሞት ይልቅ ሕይወትን፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን የመምረጥ ጥበብ ነው። የሰላም መንገድ ሁልጊዜም አሸናፊ ያደርጋል።

​👉የነገው ተስፋ አምባሳደሮች

​የሰላም ዋጋ ምን ያህል ውድ እንደሆነ ማወቅ የሚችለው የጦርነትን ጥፋት የተመለከተ ሰው ነው። ከታጣቂነት ወደ ሰላም አምባሳደርነት መምጣት ለሀገርና ለወገን ሰላም ማሰብ ነው። የበደሉትንም ሕዝብ እና ሀገር ከልብ ለመካስ ዝግጁ መሆንን ያረጋግጣል። ያነቡ እናቶችን እምባም እንደማበስ ይቆጠራል። የእናቶች እምባ የሚታበሰው በፍቅርና በመቻቻል ብቻ ነውና!

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሀገር የምታተርፈው ከሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ነው።