ሠርቶ እንጂ ነጥቆ አይከበርም።

5

 

ደብረብርሃን፡ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት በመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ያጋጠመው የሰላም ዕጦቱ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለመከወን ችግር ፈጥሮብናል ብለዋል።

ሰላም እና ልማት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች በመኾናቸው አስተማማኝ ሰላም እንዲፈጠር እንሠራለን ነው ያሉት።

የመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ አሥተዳዳሪ ኃይሌ እንግዳሰው ከተሳሳተ የሰላም ጠል አስተሳሰብ በመውጣት በርካታ ወንድሞች መንግሥት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ መቀበላቸውን ተናግረዋል።

ከወረዳው ነዋሪዎች ጋር በጋራ በመኾን ሰላም እና ልማትን ለማጠናከር በጋራ እየተሠራ መኾኑንም አንስተዋል።

ማኅበረሰባችንን ለከፋ ችግር የዳረገውን የሰላም እጦት በመቅረፍ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በጋራ መቆም እንደሚያስፈልግም የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ ዓለማየሁ አስረድተዋል።

“ሠርቶ እንጂ ነጥቆ አይከበርም” ያሉት ዋና አሥተዳዳሪው ሕዝቡ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ሰላሙን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ በበኩላቸው የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ለማረጋገጥ የጸጥታ መዋቅሩ በሚያከናውነው የሰላም ማስከበር ሥራ ላይ የሁሉም ዜጋ አበርክቶ ወሳኝ መኾኑን ገልጸዋል።

ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመፍጠርም በሚሠራው ሥራ ሰላምን ማጽናት ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ነውም ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፍቅሩ ሙልዬ የሰላም አማራጭን ተቀበለ።
Next article“ጦርነት ለማንም አይበጅም” ፍቅሩ ሙሉዬ