
ባሕር ዳር: መጋቢት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን ላሊበላ እና አካባቢው በትጥቅ ትግል ሲንቀሳስ የነበረው ፍቅሩ ሙልዬ የሰላም አማራጭን ተቀብሏል።
ላለፉት ዓመታት በሰሜን ወሎ በላሊበላ እና በአካባቢው በጫካ ሲንቀሳቀስ የነበረው ፍቅሩ ሙሉዬ የሰላም አማራጭን ተቀብሎ ለሰላም ገብቷል።
ፍቅሩ ሙልዬ በታጣቂዎች አደረጃጀት እስከ ኮር አዛዥ የደረሰ ኀላፊነት ነበረው።
በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች መካከል ተደጋጋሚ ውይይቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል። አሁንም በየአካባቢው የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ የሚገቡት ታጣቂዎች በርካታ ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
