ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ውጤቶች ተገኝተዋል።

9
አዲስ አበባ: መጋቢት 21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የብልጽግና ፓርቲ “ድምጻችን ለብልጽግናችን” በሚል መሪ መልዕክት የሴቶች እና ወጣቶች የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የኢኮኖሚ ብልጽግና ዘርፍ ሠብሣቢ መላኩ አለበል በመሠረተ ልማት፣ በማዕድን፣ በግብርና እና በሌሎችም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶች የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።
የንቅናቄ መድረኩ ለውጡን በአርዓያነት በመምራት የአሁኗን ብቻ ሳይኾን የወደፊቷንም ኢትዮጵያ ለመገንባት ወጣቶች እና ሴቶች ሚናቸውን እንዲወጡም አስቻይ መኾኑን ገልጸዋል።
ፓርቲው ሴቶችን በአመራር ሰጭነት በማሳተፍ በኢኮኖሚው ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲኾኑ የሚያስችል ሥራ መሥራቱን ተናግረዋል። ወጣቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በኢንዱስትሪ እና በግብርናው ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲኾኑ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።
ወጣቶች እና ሴቶች የፓርቲው አባላት ተልዕኮ ወስደው ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ሰላማዊ እና የሕዝብ ቅቡልነት ያለው መንግሥት እንዲመሠረት በኀላፊነት እንዲንቀሳቀሱ ዓላማ አድርጎ መድረኩ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል።
ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲደረግም የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ተሳታፊ እንዲኾኑም ጥሪ አቅርበዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የኢኮኖሚ ብልጽግና ክላስተር የፓለቲካ ዘርፍ ሠብሣቢ ጫልቱ ሳኒ ባለፉት የለውጥ ዓመታት መሠረታዊ የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል።
በተለይም የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላይ ፓርቲው የዳበረ፣ ሁሉንም ያሳተፈ እና የተሻለ ምህዳርን ገንብቷል ብለዋል።
ይሄንን ለማስቀጠል እና የፓርቲውን ራዕይ ለማሳካት ደግሞ ሴቶች እና ወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በመድረኩ የኢትዮጵያ ሴቶች እና ወጣቶች ጉዞ ከየት ወደየት በሚል ለውይይት መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
ዘጋቢ፦ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ደም አለመለገስ መድኃኒት ይዞ እንዳለመስጠት ነው” 44 ጊዜ ደም የለገሱ ባለ ታሪክ