ለጥንቃቄ፦ ለእጅ ስልክዎ (ሞባይል) ማድረግ ያለብዎት ጥንቃቄ፦

20
ባሕር ዳር: መጋቢት21/2018 ዓ.ም (አሚኮ) -ጥራት በሌላቸው ቻርጀሮች ስልክዎን ቻርጅ አያድረጉ
– ቻርጅ ሲያደርጉ የስልክዎ መሸፈኛ ወይም ከቨር ወፍራም ከኾነ ስልኩ በጣም እንዲሞቅ እና ሙቀቱ ወደ ውጭ እንዳይወጣ በመከልከል ውስጣዊ ብልሽትን ያስከትላል።
-ስልክን ፍራሽ፣ ትራስ ወይም ሶፋ ላይ አድርገው ቻርጅ አያድርጉ፦ ሙቀቱ እንዲታመቅ ስለሚያደርግ ስልኩ ከፍተኛ ሙቀት ፈጥሮ እንዲቃጥል ያደርጋል።
-የሃይል መዋዠቅ፦ (Power Surge) የኃይል በድንገት መጨመር ወይም መቀነስ ቻርጅ ላይ ያለን ስልክ የውስጥ ሰርኪዩቶቹን (Motherboard) ሊያቃጥል ይችላል።
-ቻርጅ እየተደረገ ስልኩን ለረጅም ጊዜ አይጠቀሙ፦ ስልክ ቻርጅ እያደረጉ ከባድ ጌሞችን መጫወት/ቪዲዮዎችን ማየት ባትሪው በአንድ ጊዜ ኃይል እንዲቀበልና እንዲያወጣ ስለሚያስገድደው ከፍተኛ ሙቀት ይፈጥራል።
-የተበላሸ ባትሪ ቀድሞውኑ ያበጠ፣ የፈሰሰ ወይም የተጎዳ ባትሪ ካለው ቻርጅ ሲደረግ የሚፈጠረውን ኬሚካላዊ ጫና መቋቋም ስለማይችል ሊፈነዳ ይችላል።
✍️ተጨማሪ ጥንቃቄዎች፦
👉ሁልጊዜ ለስልክዎ የራሱን ኦሪጅናል ቻርጀር ይጠቀሙ።
👉ስልኩ በጣም ከሞቀ ቻርጁን ወዲያውኑ ይንቀሉ።
👉ሌሊት ስልኩን ከራስጌዎ ስር አድርገው ቻርጅ አያድርጉ።
👉ባትሪዎ ማበጥ ከጀመረ በአፋጣኝ ይቀይሩት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleአቶ ገብረማርያም ይርጋ የዓለም አቀፉ የባሕል እና ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ኅብረት ምክትል ፕሬዝዳንት ኾነው ተሾሙ።
Next articleአካታች ፖለቲካዊ ለውጦች ለጽኑ ሀገራዊ መሠረት