የእቴጌ ጥሩወርቅ ወለባ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።

8
ባሕር ዳር: መጋቢት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በዝርፊያ ከሀገር ዉጭ ተወስዶ የነበረውን የአጼ ቴዎድሮስ ባለቤት የእቴጌ ጥሩወርቅ ውቤ ወለባ (የፀጉር ጌጥ) ተረክባለች።
በርክክቡ መርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ውጭ የተወሰዱ በርካታ ቅርሶችን ማስመለስ ተችሏል፤ ቀሪዎችንም ለማስመለስ በከፍተኛ ትኩረት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንብረት የኾኑ ነገር ግን የተዘረፉ ቅርሶቻችንን ለማስመለስ በድርድርም ኾነ በክርክር ለማስመለስ በተደረገው ጥረት እስካሁን 72 ቅርሶችን ማስመለስ መቻሉን አስታውቀዋል።
የተዘረፉ ቅርሶችን ለማስመለስ ብሔራዊ የቅርስ አስመላሽ ኮሚቴ ተቋቁሞ መሥራቱን ተናግረዋል። ኮሜቴው ሀገርን የሚያኮራ ሥራ ሠርቷል፣ እየሠራም ይገኛል ብለዋል፡፡
ይህ ቅርስ ለኢትዮጵያውያን ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት ዳይሬክተሩ ቅርሱ በብዙ ልፋት እና ውጣውረድ በባለሥልጣኑ በኢትዮጵያን ወዳጆች፣ ዜጎች እና ደርጅቶች ያለሰለሰ ጥረት ተመልሷል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት ይህንን ቅርስ እና ከዚህን በፊትም የአጼ ተዎድሮስ ጋሻ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ብለዋል። ይሄን ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በቀጣይም በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ውጭ የወጡ ቅርሶቻችንን ለማስመለስ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሚመለታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሠራ አመላክተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበሐሰተኛ መረጃ አሰራጮች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን አስታወቀ።