ሥራን ሳይንቁ ያገኙትን ዕድል ወደ ውጤት የሚለውጡ ዜጎች ይበረታታሉ።

8
አዲስ አበባ: መጋቢት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ “ከተረጂነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ መልዕክት ከ27ሺህ 872 በላይ በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ሥራ ፕሮጀክት እና ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ መርሐግብር ተጠቃሚ የኾኑ ዜጎችን አስመርቋል።
በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሥራን ሳይንቁ ለውጤት የሚተጉ ዜጎችን እናበረታታለን ብለዋል።
ይህ ተግባር ዜጎች በሀገር ግንባታ ሂደት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ዓላማ ያደረገ እንደኾነም ገልጸዋል።
የዛሬው የዜጎች ምርቃንም ተረጅነት እና ተመጽዋችነትን የማስቀረት ተግባር አንዱ አካል ነው ብለዋል።
ተመራቂዎች ያገኙትን ልምድ ተጠቅመውም የተሻለ ነገን እንዲፈጥሩም አደራ ብለዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኀላፊ ሚሊዮን ማቲዎስ ዜጎችን አብቅቶ ወደ ሥራ ማሠማራት እና አምራች ማድረግ የሰው ተኮር ልማት አንዱ መገለጫ መኾኑን ገልጸዋል።
ተመራቂዎቹ በተለማመዱት የሙያ መስክ ተሰማርተው ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን እና ሀገራቸውን ቢሮው ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
ዘጋቢ፦በለጠ ታረቀኝ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበፅኑ መሠረት ላይ እየተገነባ ያለው ዘመናዊ ከተሜነት ለትውልድ የተሻለ ኑሮ እና ለሀገር ብልጽግና መሠረት ነው፡፡