
ባሕር ዳር: መጋቢት17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የነዳጅ ጉዳይ ዓለምን እያስጨነቀ ነው። ኢትዮጵያን በመሰሉ ነዳጅን ከውጭ በሚያስገቡ ሀገራት ላይ ደግሞ ችግሩ አሳሳቢ ነው።
በአማራ ክልልም ችግሩ በተለይ በትራንስፖርት ዘርፉ ጫና እያሳደረ ነው። በክልሉ መዲና ባሕር ዳር ከወትሮው በተለየ ረጃጅም የታክሲ ሰልፎች፣ በተመሳሳይ ረጃጅም የነዳጅ ፈላጊ ተሽከርካሪዎች ሰልፍ በየቦታው እያታዩ።
ለመኾኑ ወደ ክልሉ የሚገባው የነዳጅ መጠን ቀንሷል? በምን ያህል? አሚኮ እውነታ ማጣሪያ የሚመለከተውን አካል ጠይቋል።
የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፈንታው ፈጠነ የአኹኑ የነዳጅ ውጣ ውረድ ከመካከለኛ ምሥራቅ ጦርነት ጋር በቀጥታ እንደሚያያዝ አንስተዋል። ጦርነቱ በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ጫና ማሳደሩን ገልጸዋል።
በዚህ ምክኒያት ወደ አማራ ክልል የሚገባው ነዳጅ ከግማሽ በታች ወይም ከ50 በመቶ በታች ነው ብለዋል።
ስለዚህ የቀረበውን ነዳጅ በቁጠባ መጠቀም፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ወሳኝ ተግባራት ብቻ ማዋል እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
