“የሰላምን ባሕል የሚሸረሽሩ ትርክቶችን በማረም አብሮነትን ማስቀጠል ያስፈልጋል” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)

6
ባሕር ዳር: መጋቢት 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ከወልድያ ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች ጋር በሰላም እና በልማት ዙሪያ ውይይት እያካሄዱ ነው።
የወልዲያ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ ከተማዋ የሰላም እና የልማት እንቅስቃሴዎችን አጠናክራ እንድትቀጥል የክልሉ መንግሥት ድጋፍ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።
የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ሰላም ከቤተሰብ ጀምሮ እየተኮተኮተ በማኅበረሰብ አማካኝነት እያደገ ከታሪክ፤ ከባሕል እና እምነት ጋር እየተሰናሰለ የሚገባ የችግሮች መፍቻ መንገድ ነው ብለዋል።
በሰከነ መንገድ ሐቀኛ ውይይቶችን አለማድረግ የሰላም እጦት እንዲከሰት ማድረጉን ተናግረዋል። በጫካ የሚገኙ ኃይሎች ጥያቄዎች በውይይት ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱ እያወቁ ጥያቄዎች በማይፈቱበት መንገድ መሄዳቸው የተነሱበት መንገድ ስህተት መኾኑን ያሳያል ነው ያሉት።
ሰላም ከባሕል፤ ከሃይማኖት እና ከታሪክ ጋር ግንኙነት ያለው በመኾኑ ሰላምን ማጽናት ያስፈልጋል ብለዋል። ወልድያ የሥነ መንግሥት መሠረት፤ የአብሮነት እና የአንድነት ከተማ መኾኗንም አንስተዋል።
የሰላምን ባሕል የሚሸረሽሩ፤ ከባሕል፣ ከታሪክ እና ከእሴት ጋር የማሄዱ ትርክቶችን በማረም አብሮነትን ማስቀጠል ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የከተማዋ ሰላም እንዲሰፍን፤ አልሚዎች ወደ አካባቢው እንዲመጡ፤ የመሠረተ ልማት ሥራዎች እንዲስፋፋ በዘላቂነት ሰላማችሁን ልታጸኑ ይገባል ብለዋል።
“ሰላም መቸም በጥይት አይረጋገጥም” ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ዘላቂ ሰላም እንዲጸና የከተማዋ ነዋሪዎች የበኩላችሁን ድርሻ ልትወጡ ይገባል ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየዴሞክራሲ ልምምድን ለማጎልበት የዜጎች የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።
Next article“እኛ የምንፈልገው ድጋፍን ሳይኾን አጋርነትን ነው፤ ርዳታን ሳይኾን ኢንቨስትመንትን ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ