ሀረር በሹዋሊድ በዓል ዋዜማ…

4

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሹዋሊድ በዓል በሀረሪ ክልል በየዓመቱ በድምቀት የሚከበር በዓል ነው። በበዓሉ ላይም ወጣቶችና ሴቶች አምረውና ተውበው በልዩ ድባብ የሚከበር በዓልም ነው።

የዘንድሮው ሹዋሊድ በዓል ሀረር ከተማ በኮሪደር ልማት ተውባና ደምቃ በተገኘችበት ወቅት የሚከበር መሆኑ ደግሞ ልዩ ድምቀትን ሰጥቶታል።

በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ የባህል ተቋም በዓለም ቅርስነት በተመዘገበው የሹዋሊድ የበዓል አከባበር ላይም የውጭና የሀገር ውስጥ ዜጎች ለመታደም የሰላም፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የአብሮነት ተምሳሌት በሆነችው ሀረር ከተማ መገኘታቸውን ከክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleቅድሚያ ለሰላም እንዲሰጥ አባታዊ ሚናቸውን እንደሚወጡ የወልድያ ከተማ የሃይማኖት አባቶች ተናገሩ።