
ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በጎንደር ከተማ እና አካባቢዋ እየተከናወኑ ያሉትን የልማት ተግባራት ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተው የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።
የሥራ ኀላፊዎቹ ከተጀመረ ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረውን የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት ያለበትን የአፈጻጸም ደረጃ ጎብኝተዋል።
በተጨማሪም በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ ያሉትን አምራች ኢንዱስትሪዎች እና ተገንብተው የተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ተግባራትን እንዲሁም በመገንባት ላይ የሚገኙ የኮሪደር ሥራዎችን ተዘዋውረው አይተዋል።
ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
