ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የመገጭ ግድብ ፕሮጄክትን ጎበኙ።

19
ባሕር ዳር: መጋቢት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የመገጭ ግድብ ፕሮጄክትን ጎብኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለዓመታት የተጓተቱ ፕሮጀክቶች ከጠፉበት እየተመለሱ፤ ከወደቁበት እየተነሡ ነው ብለዋል።
የሀገር ሀብት ፈሶባቸው መክነው እና ባክነው የቀሩ የኢትዮጵያ ፕሮጀክቶችን ከሞት እያስነሡ ማፋጠን የዚህ መንግሥት ልዩ መለያው ነው፡፡ የመገጭ ግድብ ደግሞ አስረጅ ምስክር ነው።
የጎንደርን የውኃ ጥም ይቆርጣል፤ የገበሬውን መሬት ያጠጣል፤ የአካባቢውን ምኅዳር ይለውጣል የተባለው የመገጭ የመጠጥ ውኃ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ ተመልክተናል ነው ያሉት።
እሱ ራሱ የጀመራቸው ብቻ ሳይኾን ተጀምረው የውልደት ስብራት የገጠማቸው ፕሮጀክቶች በብልጽግና መንግሥት አዲስ እስትንፋስ እያገኙ ግንባታቸው እየተፋጠነ ነው።
“አቁሞ ያስቀርህ እንደ መገጭ ግድብ” የሚለው ቀርቶ የአካባቢው ሰው “ወድቀህ ተነሣ እንደ መገጭ ግድብ” ብሎ መተረት ጀምሯል፤ የብልጽግና መንግሥት ብሂል ያስቀይራል ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበሐረሪ ክልል ነዳጅን በሕገ ወጥ መንገድ ሲሸጡ በተገኙ ማደያዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ።
Next article“ዘመናዊ ኑሮ ልንኖር ነው” የገጠር ኮሪደር ተጠቃሚ አርሶ አደሮች