
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሐረሪ ክልል መንግሥት ከወሰነው የነዳጅ ታሪፍ በላይ እንዲሁም ከግብይት ሰንሰለት ውጪ ሲሸጡ በተገኙ ሁለት ማደያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ አስታውቋል።
የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ኀላፊ ሸሪፍ ሙሜ እንደገለጹት ማደያዎች እርምጃ የተወደባቸው መንግሥት ከወሰነው ታሪፍ በላይ እና ከመደበኛው ገበያ ውጭ በስውር ለጥቁር ገበያ ሲሸጡ በመገኘታቸው ነው።
ማደያዎቹ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ተደጋጋሚ የጽሑፍና የቃል ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ቢሆንም ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንዳልቻሉ ኀላፊው አስረድተዋል።
በዚህም ማደያዎቹ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ምንም አይነት የነዳጅ ምርት እንዳይሸጡ መታሸጋቸውን ገልጸዋል።
በነዳጅ ግብይት ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
