
የታሪክ ማህደር፣ የኪነ-ጥበብና የሥልጣኔ መፍለቂያ በሆነችው ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ገብተናል።
ጎንደር የኢትዮጵያ የልዕልና ምልክት፣ የኅብረ-ብሔራዊነት ማሳያና ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት እንደሰምና ወርቅ ያስማማች ልዩ ከተማ ናት።
በዐፄ ቴዎድሮስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለተደረገልን እጅግ ደማቅና ክብር የተሞላበት አቀባበል ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፣ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለከተማዋ መስተዳድር የሥራ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም “እንግዳ የእግዚአብሔር ነው” በሚለው ለጋስና አስተዋይ ማንነቱ ለታወቀው ኩሩው የጎንደር ሕዝብ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
