የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አዲስ ሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሦሥተኛውን ቅርንጫፍ አስጀመረ።

23
አዲስ አበባ: መጋቢት 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አዲስ ሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሦሥተኛውን ቅርንጫፍ በልደታ ክፍለከተማ አስጀምሯል።
አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለኅብረተሰቡ ፈጣን እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መኾኑን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ከንቲባዋ የከተማ አሥተዳደሩ አዲስ ሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ሦሥተኛውን ቅርንጫፍ በልደታ ክፍለ ከተማ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል ነው ያሉት፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ትልቅ እርምጃ መኾኑን የተናገሩት ከንቲባዋ የተቀናጀ አገልግሎት ለተገልጋዩ መስጠት የሚያስችል ውጤታማ ሥራ እየተሠራበት መኾኑን ተናግረዋል።
ከተማ አሥተዳደሩ እስከሚያዝያ/2018 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሞሰብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ቅርንጫፎችን የማስፋት ሥራ እንደሚያጠናቅቅም አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ማዕከሉን በማደራጀት ወደ ሥራ መግባቱ በሀገሪቱ የታለመውን ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ ነውም ብለዋል፡፡
ማዕከሉ ቅሬታ ይቀርብባቸው የነበሩ አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል በማስገባት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ትልቅ እርምጃ ወስዷል ነው ያሉት። ሥራውም በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ትልቅ እርምጃ መኾኑን ጠቅሰዋል።
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለብዙ ጊዜ በመንግሥት ተቋማት የነበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን እየፈታ እንዳለም ተናግረዋል፡፡
ዲጂታል አንድ ማዕከል አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂን አቀናጅቶ የያዘ ትልቅ ተቋም መኾኑንም አብራርተዋል።
ሥራዎች በአግባቡ ከተመሩ ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያስመሰከርንበት ተቋም በመኾኑ ይህ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ሰለሞን አሰፌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleምስሎችን በመጠቀም የሚደርስ ሀሰተኛ የመረጃ ስርጭት፦
Next articleአሚኮ ተዓማኒነት እና ፋይዳ ያላቸው የዲጂታል ሚዲያ መረጃዎችን በማስተላለፍ ሕዝብን እያገለገለ ነው።