“ባሕርዳር የተፈጥሮ ገጸ በረከት፣ የውበት ተምሳሌት” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

5

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የተፈጥሮ ገጸ በረከት፣ የሰላምና የውበት ተምሳሌት በሆነችው፣ ታሪክን ከለመለመ ተፈጥሮ ጋር አዛምዶ በያዘው ጣና ሐይቅና በግርማዊው ዓባይ ወንዝ በታጀበችው ውቧ ባሕር ዳር ከተማ ገብተናል።

በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስንደርስ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ለካቢኔያቸው እንዲሁም ለባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አመራሮች ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

በምርቃታቸውና በጸሎታቸው ላልተለዩን ክቡራን የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም እንግዳን በፈገግታና በፍቅር መቀበል ለጋስ ማንነቱ ለሆነው ለከበረውና ለደጉ የባሕር ዳር ከተማ ሕዝብ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ።
Next articleየቁይ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ አፈጻጸም 95 ነጥብ 5 በመቶ ደርሷል።