ለሰላም አንድ ኾኖ መሥራት ይገባል።

14
ባሕር ዳር: መጋቢት 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) 1447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተከብሯል።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር እስልምና ምክር ቤት ሠብሣቢ ሼህ መሐመድ ሰኢድ ዒድ ማለት ደስታ ማለት ነው ብለዋል። በዓሉን በደስታ ማሳለፍ ይገባል ነው ያሉት።
ከራስ አልፎ በአካባቢያችሁ የሚገኙ አቅመ ደካሞችን በመርዳት እና ደስተኛ በማድረግ ልታከብሩ ይገባልም ብለዋል። የኢትዮጵያን እና የክልሉን ሰላም መጠበቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳት መሐመድ ኢብራሒም ለሰላም አንድ ኾኖ መሥራት ይገባል ብለዋል። ለሰላም ከሠራን ኢትዮጵያ ሰላም ትኾናለች ነው ያሉት።
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የዒድ አል ፈጥር በዓል መከበር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሙስሊሞች ለዓለም አንድነት እና ለሰላም እየጸለዩ ዘልቀዋል ብለዋል።
በዓሉ በዓለም ዙሪያ የሰው ልጆች ተከባብረው በአንድነት መኖር እንዳለባቸው የሚያስተምር ትምህርት ቤት መኾኑን ገልጸዋል። በዓለም ላይ ጦርነት፣ ረሃብ፣ ስደት እና ሌሎች አስከፊ ነገሮች እንዲወገዱ የሚጸለይበት የደስታ እና የምሥጋና በዓል መኾኑንም ተናግረዋል።
የከተማው ሙስሊም ማኅበረሰብ የሰላም እና የልማት አጋርነትቱን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል። የታጠቁ ኃይሎች የሚያደርሱትን ግፍ እና ውድመት ማውገዝ እና ከተጎዱ ወገኖች ጎን መኾን ይገባል ነው ያሉት።
የሀገርን ሕልውና ለማስቀጠል መንግሥት የሚያከናውነውን ተግባር እንዲደግፉም አሳስበዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ከተማ አሥተዳደሩ አግባብነታቸውን እያየ ምላሽ ለመስጠት እንደሚሠራም አስታውቀዋል።
ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የጀነት ሴት” የተባሉት ኡም አይመን በዒድ በዓል ሲታወሱ።
Next articleየመረዳዳት እና የመተሳሰብ እሴቶችን በማጠናከር በዓሉን በጋራ ማክበር ይገባል፡፡