
እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ!
በሀገራችን በድምቀት ከሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል ኢድ አል-ፈጥር አንዱ ሲኾን በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ በረመዳን ጾም ፍጻሜ የሚከበር በዓል ነው።
በዓሉ በአብሮነት፣ በምስጋና እና በደስታ የሚከበር፤ የመተሳሰብና የመፈቃቀድ ባሕልና እሴቶች የሚጠናከሩበት ታላቅ በዓል ነው።
ኢድ አል-ፈጥር የሰላምና የወንድማማችነት እሴቶችን ለመገንባት፣ የእርስበርስ ግንኙነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ያለው በዓል ነው።
የኢድ አል- ፈጥር በዓል ክፋት እና ጥላቻ በይቅርታ የሚሻሩበት፤ በአንፃሩ መልካምነት ጎልቶ የሚታይበት፣ ያለው ለሌለው በማካፈል፤ በመተሳሰብና በደስታ በድመቀት የሚከበር በዓል ነው።
ሙስሊም እህት ወድሞቻችን እንኳን ለዚህ ታላቅ ክብረ በዓል በደስታ እና በጤና አደረሳችሁ!
ኢድ-ሙባረክ!!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
