ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ለኢድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። መልእክታቸውም እንደሚከተለው ቀርቧል፦

10
እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ!
የዒድ አል ፈጥር በዓል፣ በመተባበር የደስታ ብርሃን የሚንፀባረቅበት ሕይወት በበጎነት የምትደምቅበት ታላቅ ዕለት ነው።
በታላቁ የረመዳን ወር ጾሙ ከእምነቱ በተሻገረ አስተሳስቦናል፤ ሶላቱ አቀራርቦናል፤ ኢፍጣሩ በአንድ ማዕድ ዙሪያ ሲያሰባስበን ከርሟል፤ ኢትዮጵያዊ አብሮነታችንን በተግባር አሳይቷል፡፡
ለሰው ልጆች ሁሉ ጠቃሚ የሆኑት የዒድ አል ፈጥር ዕሴቶች ለሀገር ግንባታ አስፈላጊ ዕሴቶች ናቸው። ስለሆነም በታላቁ የጾም ወቅት የተጀመረውን ኅብረት እና መተዛዘን ዘላቂነቱን ማስቀጠል ይገባል።
በታሪክ ሁሉ እንዳየነው ሀገር ያለ አብሮነት እና ያለ በጎነት ልትገነባ አትችልም፡፡ የበጎነት እጆች ችግርን ወደ ተስፋ፤ እንባን ወደ ሳቅ ይቀይራሉና ለበጎነት መበርታት ያስፈልጋል።
ኅብረ ብሔራዊ ለሆነችው ኢትዮጵያ መቻቻል እና በልዩነት ውስጥ ያለውን ውበት ጌጥ አድርጎ በዓለም ሁሉ ፊት መድመቅ ለነገይቱ ኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ነው።
የኢትዮጵያ የልማት ጉዞ ዘላቂ እንዲሆን፣ ዜጎችንም ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲያደርግ ሁላችንም ለሀገራችን የምንችለውን ሁሉ እናድርግ!
በድጋሜ መልካም የዒድ አል ፈጥር በዓል ይሁንልን።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleእንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!
Next articleኢትዮጵያ የሰላም ካባ መልበስ አለባት።