“የመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደር ሪፎርም ከፍተኛ የኾነ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና አቅም የሚጠይቅ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

12

ባሕርዳር፡ መጋቢት 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ትውውቅ እየተደረገ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የሕዝቡ የአገልግሎት ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ ይህን ፍላጎት የሚያሟላ የዘመነ የመንግሥት አገልግሎት እና አሥተዳደርን መዘርጋት አስፈላጊ መኾኑን ነው የተናገሩት።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚካሄዱ ሪፎርሞች መካከል ዛሬ እየተዋወቀ የሚገኘው ሪፎርም ሕዝብን በማገልገል በስፋቱ እና በይዘቱ ትልቁ ድርሻ የሚሰጠው እንደኾነም ጠቁመዋል።

ይህም ከፍተኛ የኾነ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና አቅም የሚጠይቅ እንደኾነም ነው የጠቀሱት።

በመድረኩ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ.ር)፣ ምክትል ኮሚሽነሮች፣ ሌሎች የፌዴራል ተቋማት የሥራ ኀላፊዎች፣ የክልሉ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመሠረተ ልማቶች እንዲገነቡ ሰላምን ማጽናት ተገቢ ነው።
Next articleየዶክተር አምባቸው መኮንን ፋውንዴሽን ጾታ ተኮር ጥቃትን ለመከላከል እና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል አዲስ ፕሮጀክት አስጀመረ።