“ገቢ የችግር መውጫ መንገዳችን ነው” መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር)

12

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በገቢ አሠባሠብ እና በአሠራሮች ዙሪያ ከወልድያ ከተማ አሥተዳደር እና ከሰሜን ወሎ ዞን የወረዳ የሥራ ኀላፊዎች እና የገቢ ተቋማት ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

የቢሮው ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) የገቢ አሠባሠብ የችግር መውጫ መንገድ ነው ብለዋል።

ከገቢ አፈጻጸም አኳያ የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ጥሩ አፈጻጸም እንዳለው በዕለቱ ተናግረዋል። የሰሜን ወሎ ዞን እና ወረዳዎች ደግሞ ዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የእኛ የገቢ አሠባሠብ በክልሉ ፕሮጀክቶች እና ሠራተኞች ላይ ተጽዕኖ አለው ያሉት ኀላፊው የክልሉን የገቢ አፈጻጸም ከፍ ለማድረግ እና መንግሥት ከእኛ የሚፈልገውን ግብ ለማሳካት ሁላችንም ጥረት ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

የክልሉን የገቢ አሠባሠብ ዕቅድ ለማሳካት በሙሉ አቅማችን እንጥራለን ነው ያሉት ዶክተር መንገሻ።

በዕለቱ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት እና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎችን አንስተዋል።

ከሰሜን ወሎ ዞን አንጻር የጸጥታ ችግሩ በሚጠበቀው ልክ ገቢ ለመሰብሰብ እንዳስቸገራቸውም ተሳታፊዎቹ መናገራቸውን ከወልድያ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሕዝብ በተግባራት ላይ እንደ ባለቤት ሲሳተፍ ሰላም ይጸናል” አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)
Next articleከፍተኛ ሙቀት የሚመዘገባቸው አካባቢዎች እና መደረግ ያለበት ጥንቃቄ፦