
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰላማዊ ኑሮን መከተል ለዘላቂ ሰላም አማራጭ የሌለው ቁልፍ መፍትሔ መሆኑን ወደሰላም የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎች ገልጸዋል። የሰላም አማራጭን መከተላቸው ለሕጋዊ ኑሮ እና ሕይወት እንደሚያበቃቸውም ተናግረዋል።
ኃይል እና ግጭት ጉዳት ከማስከተል ውጭ ሌላ ጥቅም እንዳላስገኘላቸውም አንስተዋል። ግጭት ዘላቂ መፍትሄ እንደማይኾንም ጠቁመዋል።
የማኅበረሰብ አንድነትን እና እድገት የሚመጣው በውይይት፣ በመቻቻል እና አብሮ በመኖርን ብቻ መኾኑን መገንዘባቸውንም ገልጸዋል።
አሁንም ድረስ በጫካ ያሉ ሌሎች ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀብለው እንዲመለሱም የቀድሞ ታጣቂዎች ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። ወደሰላም መመለስ ለግለሰቦች፣ ለማኅበረሰብ እና ለሀገር አጠቃላይ እድገት እንደሚጠቅም ገልጸዋል።
የጭልጋ ወረዳ አሥተዳዳሪ አዛናው አደባ፣ የወረዳው ሰላም እና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሀብታሙ እንዲነው እና ሌሎችም የወረዳው አመራሮች የቀድሞ ታጣቂዎችን መቀበላቸውን ከጭልጋ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘ መረጃ ጠቁሟል።
የወረዳው ዋና አሥተዳዳሪ አዛናው አደባ መንግሥት በማንኛውም ጊዜ ለሰላም ዝግጁ መሆኑን አስገንዝበው፣ ወደሰላም ለሚመለሱ ታጣቂዎች የሚያስፈልጉ ድጋፎች እንደሚደረጉ ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
