
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፖለቲካ፣ በንግድ፣ በኢኮኖሚ፣ በሰብዓዊ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተወያይተዋል ብሏል።
ውይይቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) በአውሮፓዊያኑ ዘመን አቆጣጠር መስከረም 2025 በሞስኮ የሥራ ጉብኝት ባደረጉት ወቅት የተደረሱ ስምምነቶችን የሚያስቀጥል መኾኑ ተገልጿል።
መሪዎቹ የኢትዮ- ሩሲያን ወዳጃዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውም ተመላክቷል።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በውይይታቸው ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች ላይ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እንደገለጹላቸውም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
