ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጋሞ ዞን በደረሰው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።

9
ባሕር ዳር: መጋቢት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በደረሰው የመንሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ፑቲን በጋሞ ዞን በተከሰተው አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የተሰማቸውን ሐዘን ለፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አስተላልፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ መልዕክት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የመሬት ናዳ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን በፍጥነት እንዲያገግሙም መልካም ምኞታቸውን ማስተላለፋቸውን በኢትዮጵያ ከሩሲያ ኢምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“የሰላም ሞተሩ ሕዝብ ነው” እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)
Next articleየክልሉ ቀዳሚ አጀንዳ ሰላም ነው።