ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አሳሰቡ።

8

 

ባሕር ዳር: መጋቢት 07/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የነዳጅ አከፋፋዮች፣ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ.ር) አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነደጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል ብለዋል። በመኾኑም ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባና ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት መጠቀም ይኖርብናል ነው ያሉት።

የነዳጅ አከፋፋዮች፣ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ፣ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በኀላፊነት ስሜት እንድንጠቀም ለማሳሰብ እወዳለው ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኮሪደር ልማት ሥራዎች ሀረር ታሪካዊ ከተማ ብቻ ሳትኾን ከዘመኑ ጋር እንደምትዘምን ያሳዩ ናቸው።