
አዲስ አበባ፡ መጋቢት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ እና ባለቤታቸው በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።
መቄዶንያ አረጋውያኑን ለመርዳት የጀመረውን የገቢ አሠባሠብ መርሐግብርም አስጀምረዋል።
ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ “መቄዶንያ የርህራሄ እና ተስፋ ለቁረጡት ተስፋን እየመለሰ የሚገኝ ማዕከል ነው” ብለዋል።
መንግሥት ለአረጋውያኑ ከሚያደርገው የመቋቋሚያ ድጋፍ መርሐግብር በተጨማሪ ግለሰቦች እና ድርጅቶች አረጋውያንን መርዳታቸው ወገናዊ ኀላፊነትን መወጣት ነው ብለዋል።
የመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል ከ9ሺህ በላይ አረጋውያንን እና የአዕምሮ ህሙማንን እያገዘ ይገኛል።
መቄዶንያ በኢትዮጵያ በ56 ከተሞች ማዕከል የከፈተ ሲኾን በ14 ከተሞች ሕንጻ እየገነባም ይገኛል።
በተመሥገን ዳረጎት
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
