በቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮጀክት 1 ሺህ 589 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ተሸፍኗል።

3

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል እና የዞን መሪዎች በራያ ቆቦ ተገኝተው በቆቦ ጊራና ሸለቆ ልማት ፕሮግራም ጽሕፈት ቤት እየተከናወኑ ያሉ የመስኖ ልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር)፣ በሰሜን ወሎ ዞን የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ከድር ሙስጦፋ እና የወረዳዉ አመራሮች ናቸው ልማቱን ተዘዋውረው የተመለከቱት።

በሆርማት ጎሊና ቁጥር 6 መስኖ ፕሮጀክት ላይ ባደረጉት የመስክ ምልከታ የሰብሉ ቁመና ለውጤት የሚያበቃ ስለመኾኑ ገልጸዋል።

ጽሕፈት ቤቱ ከቆቦ እስከ ሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ድረስ ያለውን ሰፊ የከርሰ ምድር ውኃ ሃብት ለዘመናዊ መስኖ ልማት በማዋል ላይ ይገኛል።

​በአሁኑ ወቅት ወደ ሥራ በገቡ 42 የመስኖ ፕሮጀክቶች 1 ሺህ 589 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች፣ አትክልት እና ቋሚ ፍራፍሬዎች እየለማ ይገኛል።

በተለይም በዚህ የምርት ዘመን ​ከ530 ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ሰብል ሲሸፈን ​በአሁኑ ወቅት የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ ሥራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ቀሪው ሰብልም በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል። ​

የመስኖ ልማቱ ከዚህ በበለጠ እንዲሰፋና አርሶ አደሮች ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲኾኑ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበፍቅር እና በአንድነት በመቆም የሀገርን ሰላም እና ልማት ማስቀጠል ይገባል።
Next article“መቄዶንያ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋን የመለሰ ማዕከል ነው” ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ