የፊጣራ ሥነ ሥርዓት በፊቼ ጨምባላላ ዋዜማ ተካሄደ።

2

 

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ “የፊቼ ጫምባላላ” በዓልን የሚቀበልበት የዋዜማ ምሽት የ”ፊጣራ” ሥርዓት “ሻፌታ” ቀርቦ በሀገር ሽማግሌዎች ተመርቆ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

በፊጣራ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ነገ በማለዳው ደግሞ ሕዝቡ ወደ “ሶሬሳ ጉዱ ማሌ” በመትመም አዲሱን ዓመት የሚቀበልበት በዓል ይጠበቃል።

ዘጋቢ፦ ድልነሳ መንግሥቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ፊቼ ጫምባላላን ስናከብር አንድነት እና ኅብረታችንን በማጠናከር ሊኾን ይገባል” የሲዳማ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ