
አዲስ አበባ: መጋቢት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአስተርጓሚ እና አሳታሚ ዶክተር መሠረት መንግሥቱ “እቴጌ ጣይቱ እና ዳግማዊ ምኒልክ ኢትዮጵያ 1883 እስከ 1910 እ.ኤ.አ” በሚል የታተመው መፅሐፍ ተመርቋል።
መጽሐፉ ክሪስ ፕራውቲ በእንግሊዝኛ የጻፈችው ሲኾን በሕይወት ተፈራ እና ዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ የተተረጎመ ነው።
የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የማይበገር ማንነት ማኅተም፤ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ፋና እና የሰው ልጅ እኩልነት የተረጋገጠበት ነው።
መጽሐፉ የዓድዋን ዓለም አቀፋዊ ድልነት ለትውልዱ ለማስተማር እንደሚያግዝም ተገልጿል።
በምርቃቱ ላይ የተገኙት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ዛሬ እንዲህ በኩራት እንድንገኝ ያደረገን እና የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የኾነው በዓድዋ ድል ጀግኖች ነው ብለዋል።
መጽሐፉ ትክክለኛ ታሪክን የሰነደ፣ ለአሁኑም ኾነ ለቀጣዩ ትውልድ ጀግንነትን የሚያስተምር እንደኾነ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ኢብራሒም መሐመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
