የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ያደናቅፋል።

5

 

ባሕር ዳር:መጋቢት 5/2018 ዓ.ም ማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ጨምሮ በተለያዩ የሚድያ አውታሮች የሚሰራጩ መረጃዎች ትክክለኛነታቸው እና ተዓማኒነታቸው ካልተረጋገጠ በሀገር ላይ የሚስከትሉት ቀውስ የከፋ ነው።

ለአሚኮ አስተያየታቸውን የሰጡ የምሥራቅ ጎጃም ዞን የመንግሥት ሠራተኞች በተለያዩ መንገዶች የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች በሰላም ግንባታ እንዲኹም በልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳርፉ አንስተዋል፡፡

በተለያየ ጊዜ የሚለቀቁ መረጃዎችን ትክክለኛነት ማረጋገጥና ከትክክለኛ የመረጃ ምንጭ የሚወጡ መረጃዎችን ማየትና ማጋራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚያስከትለውን ኹለንተናዊ ጉዳት በመከላከልና ትክክለኛ መረጃ ለኅብረተሰቡ እንዲደርስ በማድረግ በኩል ምሁራንና የመንግሥት ሠራተኞች ኅላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ጠይቀዋል፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋዬ በላይ ሕዝብን የሚያደናግሩና በሕዝቦች መካከል መጠራጠርን የሚያስከትሉ ሐሰተኛ መረጃዎችን በመከላከል ረገድ የመንግሥት ሠራተኞች ኅላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት የሰላም ግንባታ ሥራዎችን የሚያደናቅፍ ናቸው ብለዋል። የመንግሥት ሠራተኞች ኅብረተሰቡን በማንቃት መንግሥት የጣለባቸውን ኅላፊነት በአግባቡ እንዲወጡም አስገንዝበዋል፡፡

በዜጎች የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድረውን የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣም ተጠይቋል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፍቅር እና ሰላም የሚሰበክበት ፊቼ ጫምባላላ!
Next articleውጤታማ የልማት ተግባራት እየተከናወኑ መኾኑን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።