ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ተጎጅዎች የሚደረገው ድጋፍ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ።

8

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ እና ሌሎች ወረዳዎች ተገኝተው ተጎጅዎችን እያጽናኑ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባጋሩት መልእክትም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ እና ሌሎች ወረዳዎች በበልግ ዝናብ ምክንያት በተከሠተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸው ላለፈ ዜጎቻችን የተሰማኝን ኀዘን እገልጻለሁ ብለዋል። “መንግሥት ለተጎጂ ወገኖቻችን አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል” ሲሉም አረጋግጠዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ተገቢው ጥናትና ሥራ መከናወን አለበት፤ የጥንቃቄ ተግባራትም አስፈላጊዎች ናቸው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየክልሉ መንግሥት የዋግኽምራ ሕዝብ የልማት ጥያቄዎችን እየመለሰ መኾኑን ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next articleፍቅር እና ሰላም የሚሰበክበት ፊቼ ጫምባላላ!