ለጥንቃቄ፦ በድምጽ ጥሪ አማካኝነት የሚፈጸም የሳይበር ጥቃት፦

8

 

ባሕር ዳር: መጋቢት05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቪሺንግ(Vshing) መረጃ በማጥመድ ከሚፈጸሙ የጥቃት አይነቶች አንዱ ነው። በድምጽ ጥሪ አማካኝነት የሚፈጸም የጥቃት ዓይነት ነው።

አጭበርባሪዎች ሕጋዊ አካል መስለው ስልክ በመደወል የግለሰቦችን የግል መረጃዎች፣ የይለፍ ቃሎች፣ የክሬዲት ካርድ ቁጥሮችን እና ሌሎች መሰል ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመመንተፍ ይህን የጥቃት አይነት ይጠቀማሉ።

የዚህ አይነት ማጭበርበር በእውነተኛ ሰዎች ወይም አስቀድሞ በተቀዳ ሮቦ-ኮሎች (robocalls) የሚፈጸም ነው።

በመኾኑ ከማያውቁት አካል ለሚደረግ የስልክ ጥሪ የትኛውንም መረጃ ከመስጠት መቀጠብ ተገቢ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአሚኮ ከአልማኮን ሕንጻ ተቋራጭ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ወደ አርባምንጭ አቅንተዋል።