ኪነ ጥበብ ኢትዮጵያዊነትን ለማጽናት እና ለማነጽ ሚናው ከፍተኛ ነው።

9

 

አዲስ አበባ፡ መጋቢት 05/2018 ዓ.ም(አሚኮ) 17ኛው ከተማ አቀፍ አዲስ የኪነጥበብ ፌስቲቫል ሳምንት ተከፍቷል።

ፌስቲቫሉ ከመጋቢት 5/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 7/2018 ዓ.ም እንደሚቆይም ተገልጿል። “የጥበብ ስጦታ ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ መልዕክት ነው የሚካሄደው።

የአዲስ አበባ ከተማ ባሕል እና ኪነጥበብ ቢሮ ኀላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ.ር) ኪነ ጥበብ ኢትዮጵያዊነትን ለማጽናት እና ለማነጽ ሀገርንም ለማሻገር ሚናው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ኪነ ጥበብ ማኅበራዊ አገልግሎት ብቻ ሳይኾን ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቱም የማይተካ ነው ያሉት ኀላፊዋ በመዲናዋ ዜጎች ኢትዮጵያዊነትን አክብረው እንዲኖሩ ኪነጥበብ ላይ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ እንደኾነ ጠቁመዋል።

የኪነ ጥበብ ፌስቲቫሉ በየዓመቱ እያደገ በመምጣቱ ዕድገቱን በማሳለጥ ከከተማነት ባለፈ ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የመኾን ዕድሉን ለማስፋት እና ተደራሽነቱን ለማረጋገጥ እንሠራለን ብለዋል።

ኪነ ጥበብ ማንነታችንን በመግለጽ ባሕል፣ ታሪክ እና እሴትን ለማጉላት የጎላ ሚና አለው ነው ያሉት።

ኪነ ጥበብን ልንጠብቀው ልናከብረው እና ለቀጣይ ዘመናት በክብር ልናሻግረው ይገባል ብለዋል። በዘመናት መለዋወጥ እና በቴክኖሎጂ ዕድገት ሳቢያ የሚከሰቱ መጤ ባሕሎችን በመቅረፍ ከሀገር ባሕል እና እሴት ጋር አጣጥሞ ማሻገር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የዘመናዊነት እሳቤንም እኛነታችን ሳይደበዝዝ እና ሳይጠፋ በመቀበል በማጣጣም መሥራት ይገባናል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሀገር በትብብር ትገነባለች።
Next articleአሚኮ ከአልማኮን ሕንጻ ተቋራጭ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።