ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)ከሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱም ጋር ተወያዩ።

18

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 05/2018 ዓ.ም(አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱም ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የዱባይ ገዢ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ግርማዊ ሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱምን አግኝቼ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

‎በሁለቱ ሀገራት እና ሕዝቦች መካከል ስላለው ጠንካራ የቢዝነስ፣ ትምህርት እና ባሕል ትስስር መነጋገራቸውን ገልጸዋል። ከዚህች ጠንካራ፣ ውብ እና ጽኑ ከተማ ጋር ያለን ትስስር በቀጣይ ጉብኝቶችም ይጠናከራል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ፍቼ ጫምባላላ የኢትዮጵያችን አንዱ ውብ ቀለም ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleሀገር በትብብር ትገነባለች።