“ፍቼ ጫምባላላ የኢትዮጵያችን አንዱ ውብ ቀለም ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

15

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 05/2018 ዓ.ም(አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ነው ያሉት።

ፍቼ ጫምባላላ የሲዳማ ሕዝብ ማንነት መገለጫ፣ የኢትዮጵያችን ደግሞ አንዱ ውብ ቀለም ነው ብለዋል።

ይህ በዓል የሰላምና የዕርቅ ዋዜማ፣ የፍቅርና የአንድነት ማሳያ ነው። ያለፈውን በይቅርታ ትተን፣ አዲሱን ዘመን በአዲስ ተስፋና በታላቅ ራዕይ ለመቀበል ሁላችንም በአንድነት የምንቆምበት ወቅት ነው።

ዘመኑ የሰላም፣ የጤናና የብልጽግና ይሁንልን። በድጋሜ እንኳን ለፍቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አይዴ ጫምባላላ ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleምርጫ ቦርድ በስምረት ፓርቲ በኩል ቀርቦ የነበረው የክስ ፋይል መዘጋቱን አስታወቀ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)ከሼኽ ሞሃሙድ ቢን ራሺድ አል መክቱም ጋር ተወያዩ።