
አዲስ አበባ፡ መጋቢት 04/2018 ዓ.ም(አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሠብሣቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የመራጮች ምዝገባ ከተጀመረበት ከየካቲት 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደ የሰባት ቀናት ምዝገባ ከ9 ሚሊዮን 36ሺህ በላይ መራጮችን መመዝገብ ተችሏል ብለዋል።
በጠቅላላ ካሉት 52ሺህ 773 የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ 6ሺህ 395 ጣቢያዎች ሥራ አልጀመሩም ነው ያሉት።
ዋና ምክንያቱ ደግሞ ከመራጮች ምዝገባ ጋር በተገናኘ በቁሳቁስ ስርጭት ችግር መኾኑን ጠቁመዋል።
ፓርቲዎች የሚያደርጉትን ክርክር ከሚዲያ፣ ከትምህርት ተቋቀማት እና ከምርምር ተቋማት ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተገመገመ ነው ብለዋል።
ኮሚቴው በዋናነት የፓርቲዎቹ የሀሳብ ሁኔታ ጠቃሚነት እና የመረጃዎቻቸውን እውነታነት ያጣራል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
