ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጋሞ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።

20
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 04/2018 ዓ.ም(አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጋሞ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ በዜጎቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማኝን ጥልቅ ልባዊ ሐዘን ለመግለፅ እወዳለሁ ብለዋል።
በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው የተጎጂ ቤተሰቦች እና ዘመድ ወዳጆች ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁ ነው ያሉት።
በቀጣይም በአደጋው ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም የጉዳቱን ሰለባዎች ለመርዳት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleደም መለገስ ሕይወትን የማዳን ቅዱስ ተግባር ነው።
Next articleበኢትዮጵያ ያለው የመረጃ አጠቃቀም እና የማጣራት ክህሎት ምን ይመስላል?