
ባሕር ዳር: መጋቢት 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ የታሪክ እስረኛ አይደለችም፤ ይልቁንም የበደሏትን ይቅር ብላ፣ የወደዷትን አክብራ፣ እንኳን ለራሷ ለቀጣናው ከሚተርፈው ሰፊ ገበታዋ ለማቋደስ በፈጣን የልማት ጎዳና ላይ የምትታትር ታላቅ ሀገር ናት ነው ያሉት።
እያንዳንዱ ቀን የሀገሬን እና የሕዝቤን ታላቅነት ሳያረጋግጥ አይባክንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተዘዋውሬ በጎበኘኋቸው አካባቢዎች እና ባገኘኋቸው አጋጣሚዎች በማገኛቸው የሀገሬ ልጆች ዓይን ውስጥ የማየው ተስፋ ሁሌም የሚያተጋኝ አቅሜ ነው ብለዋል።
ሁላችንም በተሰማራንበት ዘርፍ ሁሉ ከፍ ላለው ውጤት እንትጋ፤ ኢትዮጵያ ከሆነችው በላይ ታላቅ የምትሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለምና ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
